1 ወርቁ እንዴት ደበሰ!ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ!የከበሩ ድንጋዮች፣በየመንገዱ ዳር ተበታትነዋል።
2 እንደ ወርቅ ይቈጠሩ የነበሩ፣የከበሩ የጽዮን ወንዶች ልጆች፣የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው፣እንዴት አሁን እንደ ሸክላ ዕቃ ሆኑ!
3 ቀበሮዎች እንኳን ግልገሎቻቸውን ለማጥባት፣ጡታቸውን ይሰጣሉ፤ሕዝቤ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች፣ጨካኞች ሆኑ።
4 ከውሃ ጥም የተነሣ፣የሕፃናት ምላስ ከላንቃቸው ጋር ተጣበቀ፤ልጆቹ ምግብ ለመኑ፤ነገር ግን ማንም አልሰጣቸውም።
5 ምርጥ ምግብ ይበሉ የነበሩ፣ተቸግረው በየመንገዱ ላይ ተንከራተቱ፤ሐምራዊ ግምጃ ለብሰው ያደጉ፣አሁን በዐመድ ክምር ላይ ተኙ።
6 በሕዝቤ ላይ የደረሰው ቅጣት፣የማንም እጅ ሳይረዳት፣በድንገት ከተገለበጠችው፣ሰዶም ላይ ከደረሰው ቅጣት ይልቅ ታላቅ ነው።