2 ርስታችን ለመጻተኞች፣ቤቶቻችን ለባዕዳን ዐልፈው ተሰጡ።
3 ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው ሆንን፤እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።
4 ለምንጠጣው ውሃ መክፈል ነበረብን፤ዕንጨታችንንም የምናገኘው በግዢ ነበር።
5 የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤ተጨንቀናል ዕረፍትም አጥተናል።
6 እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ለአሦርና ለግብፅ እጃችንን ሰጠን።
7 አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው አለፉ፤እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።
8 ባሮች ሠልጥነውብናል፤ከእጃቸው ነጻ የሚያወጣን ማንም የለም።