4 ለምንጠጣው ውሃ መክፈል ነበረብን፤ዕንጨታችንንም የምናገኘው በግዢ ነበር።
5 የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤ተጨንቀናል ዕረፍትም አጥተናል።
6 እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ለአሦርና ለግብፅ እጃችንን ሰጠን።
7 አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው አለፉ፤እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።
8 ባሮች ሠልጥነውብናል፤ከእጃቸው ነጻ የሚያወጣን ማንም የለም።
9 በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሣ፣በሕይወታችን ተወራርደን እንጀራ አገኘን።
10 ቈዳችን እንደ ምድጃ ጠቍሮአል፤በራብም ተቃጥሎአል።