22 ፈላጥያ፣ ሐናን፣ ዓናያ፣
23 ሆሴዕ፣ ሐናንያ፣ አሱብ፣
24 አሎኤስ፣ ፈልሃ፣ ሶቤቅ፣
25 ሬሁም፣ ሐሰብና፣ መዕሤያ፣
26 አኪያ፣ ሐናን፣ ዓናን፣
27 መሉክ፣ ካሪምና በዓና።
28 የቀሩት ሕዝብ፦ ማለት ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑ፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ስለ እግዚአብሔር ሕግ ብለው ራሳቸውን ከጎረቤት አሕዛብ የለዩ ሁሉ፣ ሚስቶቻቸው፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፣ የሚያውቁና የሚያስተውሉ ሁሉ ቃለ መሐላ ፈጸሙ፤