1 ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የተመለሱት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣
2 አማርያ፣ መሉክ፣ ሐጡስ፣
3 ሴኬንያ፣ ሬሁም፣ ሜሪሞት፣
4 አዶ፣ ጌንቶን፣ አብያ፣
5 ሚያሚን፣ መዓድያ፣ ቢልጋ፣
6 ሸማያ፣ ዮያሪብ፣ ዮዳኤ፣
7 ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ።እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ።