18 ከቢልጋ፣ ሳሙስ፤ከሸማያ፣ ዮናታን፤
19 ከዮያሪብ፣ መትናይ፤ከዮዳኤ፣ ኦዚ፤
20 ከሳላይ፣ ቃላይ፤ከዓሞቅ፣ ዔቤር፤
21 ከኬልቅያስ፣ ሐሸብያ፤ከዮዳኤ፣ ናትናኤል።
22 በኤሊያሴብ፣ በዮአዳ፣ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆችና ካህናቱ፣ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር።
23 ከሌዋውያን ዘሮች መካከል እስከ ኤሊያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ድረስ ያሉት የየቤተ ሰቡ ኀላፊዎች በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር።
24 የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር።