ነህምያ 12:24-30 NASV

24 የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር።

25 በቅጥሩ በሮች አጠገብ ያሉትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁት ዘቦች ደግሞ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም፣ ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ።

26 እነዚህም በኢዮሴዴቅ ልጅ፣ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም፣ በአገረገዢ በነህምያ፣ በካህኑና በጸሓፊው በዕዝራ ዘመን አገለገሉ።

27 የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ሌዋውያኑ በምስጋና መዝሙር፣ በጸናጽል፣ በበገናና በመሰንቆ ድምፅ የምረቃውን በዓል በደስታ እንዲያከብሩ ከሚኖሩበት ተፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

28 መዘምራኑንም እንደዚሁ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለው ከነጦፋውያን መንደሮች በአንድነት ሰበሰቧቸው።

29 በኢየሩሳሌም ዙሪያ የራሳቸውን መንደሮች ሠርተው ስለ ነበር፣ መዘምራኑን ያመጧቸው ከቤት ጌልገላ፣ ከጌባና ከዓዝምት አካባቢ ነው።

30 ካህናቱና ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ካነጹ በኋላ፣ ሕዝቡን፣ ቅጥሩና በሮቹን አነጹ።