ናሆም 2:7-13 NASV

7 ከተማዪቱ መማረኳና መወሰዷ እንደማይቀር፣አስቀድሞ ተነግሮአል፤ሴቶች ባሪያዎቿ እንደ ርግብ ያለቅሳሉ፤ደረታቸውንም ይደቃሉ።

8 ነነዌ እንደ ኵሬ ናት፤ውሃዋም ይደርቃል፤“ቁም! ቁም!” ብለው ይጮኻሉ፤ነገር ግን ወደ ኋላ የሚመለስ የለም።

9 ብሩን ዝረፉ፤ወርቁን ንጠቍ፤በየግምጃ ቤቱ ያለው፤የተከማቸውም ሀብት ስፍር ቍጥር የለውም።

10 ተበዝብዛለች፤ ተዘርፋለች፤ ተራቍታለች።ልብ ቀልጦአል፤ ጒልበት ተብረክርኮአል፤ሰውነት ተንቀጥቅጦአል፤ ፊት ሁሉ ገርጥቶአል።

11 አሁን ታዲያ የአንበሶቹ ዋሻ፣ደቦሎቻቸውን ያበሉበትወንዱና ሴቷ አንበሳ የሄዱበት፣ግልገሎችም ሳይፈሩ የተሰማሩበት ቦታ ወዴት ነው?

12 አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃውን ያህል ገደለ፤ለእንስቶቹም ዐንቆ ገደለላቸው፤የገደለውን በማረፊያ ቦታው፣የነጠቀውንም በዋሻው ሞልቶታል።

13 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በእናንተ ላይ ተነሥቼባችኋለሁ፤ሠረገሎቻችሁን አቃጥዬ አጨሳለሁ፤ደቦል አንበሶቻችሁን ሰይፍ ይበላል፤የምትበሉትን በምድር ላይ አልተውላችሁም፤የመልእክተኞቻችሁም ድምፅ፣ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።”