አብድዩ 1:12-18 NASV

12 ክፉ ቀን በገጠመው ጊዜ፤በወንድምህ ሥቃይ መደሰት አልነበረብህም፤በጥፋታቸው ቀን፣ የይሁዳ ሕዝብ ሲያዝኑሐሤት ማድረግ አልነበረብህም፤በጭንቀታቸውም ቀን፣በትዕቢት ልትናገር አይገባህም ነበር።

13 በጥፋታቸው ቀን፣በሕዝቤ በር መግባት የለብህም ነበር፤በጥፋታቸው ቀን፣በጭንቀታቸው መደሰት አልነበረብህም፤በጥፋታቸው ቀን፣ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር።

14 ስደተኞቻቸውን ለመግደል፣በመንታ መንገድ መጠባበቅ አይገባህም ነበር፣በጭንቀታቸው ቀን፣የተረፉትን አሳልፈህ መስጠት አልነበረብህም።

15 “በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ የእግዚአብሔር ቀን ደርሶአል፤አንተ እንዳደረግኸው፣ በአንተም ላይ ይደረጋል፤ክፉ ሥራህም በራስህ ላይ ይመለሳል።

16 እናንተ በቅዱሱ ተራራዬ እንደ ጠጣችሁ፣አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ፤ይጠጣሉ፤ አብዝተውም ይጠጣሉ፤ከዚህም በፊት እንዳልሆኑት ይሆናሉ።

17 ነገር ግን በጽዮን ተራራ ነጻ መውጣት ይሆናል፤የያዕቆብ ቤትም እርሷ የተቀደሰች ትሆናለች፤ርስታቸውን ይወርሳሉ።

18 የያዕቆብ ቤት እሳት፣የዮሴፍም ቤት ነበልባል ይሆናል፤የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናል፤ያቃጥሉታል፤ ይበሉትማል፤ከዔሳው ቤት የሚተርፍ፣ አይኖርም።” እግዚአብሔር ተናግሮአል።