1 በመጠበቂያ ላይ እቆማለሁ፤በምሽጒ ቅጥር ላይ ወጥቼ እቈያለሁ፤ምን እንደሚለኝ፣ለክርክሩም የምሰጠውን መልስ ለማወቅ እጠባበቃለሁ።
2 እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፤“በቀላሉ እንዲነበብ፣ራእዩን ጻፈው፤በሰሌዳም ላይ ቅረጸው።
3 ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃልና፤ስለ መጨረሻውም ይናገራል፤እርሱም አይዋሽም፤የሚዘገይ ቢመስልም ጠብቀው፤በርግጥ ይመጣል፤ ከቶም አይዘገይም።
4 “እነሆ፤ እርሱ ታብዮአል፤ምኞቱ ቀና አይደለም፤ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል።
5 በእርግጥ የወይን ጠጅ አታሎታል፤ትዕቢተኛ ነው፤ ከቶ አያርፍም፤እንደ ሲኦል ስስታም ነው፣እንደ ሞት ከቶ አይጠግብም፤ሕዝቦችን ለራሱ ይሰበስባል፤ሰዎችንም ሁሉ ማርኮ ይወስዳል።