11 ድንጋይ ከቅጥሩ ውስጥ ይጮኻል፤ከዕንጨት የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይመልሱለታል።
12 “ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚሠራ፣በወንጀልም ለሚመሠርታት ወዮለት።
13 ሰዎች ለእሳት ማገዶ እንዲሆን እንዲለፉ፣ሕዝቦችም በከንቱ እንዲደክሙ፣ እግዚአብሔር ጸባኦት ወስኖ የለምን?
14 ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን ሁሉ፣ምድርም የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።
15 “ኀፍረተ ሥጋቸውን ለማየት፤ባልንጀሮቹን ለሚያጠጣ፣እስኪሰክሩም ድረስ ወይን ለሚቀዳላቸው ወዮለት!
16 በክብር ፈንታ ዕፍረት ትሞላለህ፤አሁን ደግሞ ተራው የአንተ ነውና፤ ጠጣ፤ ኀፍረተ ሥጋህም ይገለጥ፤ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ይመለስብሃል፤ክብርህንም ውርደት ይሸፍነዋል።
17 በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ያጥለቀልቅሃል፤እንስሳቱን ማጥፋትህም ያስደነግጥሃል፤የሰው ደም አፍሰሃልና፤አገሮችንና ከተሞችን በውስጣቸው የሚኖሩትንም ሁሉ አጥፍተሃልና።