16 እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤እግሬም ተብረከረከ፤ሆኖም በሚወረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።
17 ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣የበጎች ጒረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣
18 እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤በድነቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
19 ጌታ እግዚአብሔር ኀይሌ ነው፤እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።ለመዘምራን አለቃ፣ በባለ አውታር መሣሪያዎቼ የተዘመረ መዝሙር።