1 ስለዚህ መታገሥ ስላልቻልን ለጊዜው በአቴና ብቻችንን መቅረት መልካም መስሎ ታየን።
2 በእምነታችሁ እንዲያጸናችሁና እንዲያበረታችሁ ወንድማችንንና በክርስቶስ ወንጌል ሥራ ከእኛ ጋር የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤
3 ይኸውም በዚህ ፈተና ማንም እንዳይናወጥ ነው። እኛም ለዚህ ነገር እንደ ተመደብን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
4 በርግጥ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ መከራ እንደሚደርስብን በየጊዜው እንነግራችሁ ነበር፤ እንደምታውቁትም እንዲሁ ደግሞ ሆኖአል።