15 ማንም በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁል ጊዜ መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።
16 ሁል ጊዜ ደስ ይበላችሁ፤
17 ሳታቋርጡ ጸልዩ፤
18 በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።
19 የመንፈስን እሳት አታዳፍኑ፤
20 ትንቢትን አትናቁ።
21 ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ፤