1 ጢሞቴዎስ 6:12-18 NASV

12 መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ በብዙ ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትንና የተጠራህበትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ።

13 ለሁሉም ሕይወትን በሚሰጥ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁም በጳንጥዮስ ጲላጦስ ፊት እውነትን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት ዐደራ የምልህ፣

14 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ፣ ይህን ትእዛዝ ያለ ዕድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ እንድትጠብቅ ነው፤

15 ያም መገለጥ፣ የተባረከውና ብቻውን ገዥ የሆነው የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ የሚያሳየው ነው፤

16 እርሱ ብቻ ኢመዋቲ ነው፤ ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤ እርሱን ያየ ማንም የለም፤ ሊያየውም የሚችል የለም። ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤ አሜን።

17 በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።

18 መልካም እንዲሠሩ፣ ቸሮችና ለማካፈል ፈቃደኞች የሆኑ እንዲሆኑ እዘዛቸው።