1 ጌቶች ሆይ፤ እናንተም በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ስለምታውቁ አገልጋዮቻችሁን በፍትሕና በቅንነት አስተዳድሯቸው።
2 ከማመስገን ጋር ነቅታችሁ በትጋት ጸልዩ።
3 እኔ እስረኛ የሆንሁለትን የክርስቶስን ምስጢር ማወጅ እንድንችል፣ እግዚአብሔር የቃሉን በር እንዲከፍትልን ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤
4 ደግሞም መናገር እንደሚገባኝ ቃሉን በግልጽ እንድናገር ጸልዩልኝ።