1 የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፤ለውድ ወዳጃችንና አብሮን ለሚሠራው ለፊልሞና፣
2 ለእኅታችን ለአፍብያ፣ አብሮን ወታደር ለሆነው ለአርክጳ በቤትህም ላለችው ቤተ ክርስቲያን፤
3 ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
4 አንተን በጸሎቴ በማስብህ ጊዜ ዘወትር አምላኬን አመሰግናለሁ፤
5 ምክንያቱም በጌታ በኢየሱስ ያለህን እምነትና ለቅዱሳንም ሁሉ ያለህን ፍቅር ሰምቻለሁ።