16 “በዚያ ቀን፣ ‘ባሌ’ ብለሽ፣ትጠሪኛለሽ” ይላል እግዚአብሔር።“ከእንግዲህም፣ ‘ጌታዬ’ ብለሽ አትጠሪኝም።
17 የበኣል አማልክትን ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ስሞቻቸው አይነሡም።
18 በዚያን ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፣በምድርም ላይ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረት ጋር፣ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ፤ሁሉም በሰላም እንዲኖሩ፣ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን፣ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።
19 ለእኔ እንድትሆኚ ለዘላለም አጭሻለሁ፤በጽድቅና በፍትሕ፣በፍቅርና በርኅራኄም አጭሻለሁ።
20 በታማኝነት አጭሻለሁ፤አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።
21 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በዚያ ቀን እኔ እመልሳለሁ፤ለሰማያት እመልሳለሁ፤እነርሱም ለምድር ምላሽ ይሰጣሉ፤
22 ምድርም ለእህል፣ለአዲስ የወይን ጠጅና ለዘይት ምላሽ ትሰጣለች፤እነርሱም ለኢይዝራኤል ምላሽ ይሰጣሉ።