1 መሳፍንት በሚገዙበት ዘመን፣ በምድሪቱ ላይ ራብ ሆነ፤ አንድ ሰው በይሁዳ ከምትገኘው ከቤተ ልሔም ሚስቱንና ሁለቱን ወንዶች ልጆቹን ይዞ፣ ለተወሰነ ጊዜ ለመኖር ወደ ሞዓብ አገር ሄደ።
2 የሰውየው ስም አቤሜሌክ፣ የሚስቱ ኑኃሚን፣ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበሩ። እነርሱም የይሁዳ ቤተ ልሔም ኤፍራታውያን ሲሆኑ፣ ወደ ሞዓብ አገር ሄደው በዚያ ኖሩ።
3 የኑኃሚን ባል አቤሜሌክ ሞተ፤ ኑኃሚንም፣ ከሁለት ልጆቿ ጋር ብቻዋን ቀረች።
4 ልጆቿም ዖርፋና ሩት የተባሉ የሞዓብ ሴቶችን አገቡ፤ በዚያም ዐሥር ዓመት ያህል ከኖሩ በኋላ፣
5 መሐሎንና ኬሌዎን ሁለቱም ሞቱ፤ ኑኃሚንም ሁለት ልጆቿንና ባሏን አጥታ ብቻዋን ቀረች።