2 አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም፣እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ፣ እግዚአብሔር የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል።
3 የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፤ተዋጊዎቹ ቀይ ልብስ ለብሰዋል፤ዝግጁ በሆኑበት ቀን፣የሠረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል፤የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል።
4 ሠረገሎች በአደባባይ ወዲያ ወዲህ ይከንፋሉ፤በመንገዶችም ላይ ይርመሰመሳሉ፤የሚንበለበል ፋና ይመስላሉ፤እንደ መብረቅም ይወረወራሉ።
5 ምርጥ ተዋጊዎቹን ይጠራል፤ዳሩ ግን መንገድ ላይ ይሰናከላሉ፤ወደ ከተማዪቱ ቅጥር ይሮጣሉ፤መከላከያ ጋሻውም በቦታው አለ።
6 የወንዙ በር ወለል ብሎ ተከፈተ፤ቤተ መንግሥቱም ወደቀ።
7 ከተማዪቱ መማረኳና መወሰዷ እንደማይቀር፣አስቀድሞ ተነግሮአል፤ሴቶች ባሪያዎቿ እንደ ርግብ ያለቅሳሉ፤ደረታቸውንም ይደቃሉ።
8 ነነዌ እንደ ኵሬ ናት፤ውሃዋም ይደርቃል፤“ቁም! ቁም!” ብለው ይጮኻሉ፤ነገር ግን ወደ ኋላ የሚመለስ የለም።