12 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም ጀምሮ ያለህ አይደለህምን?የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ እኛ አንሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርዱ ሾመሃቸዋል፤ዐለት ሆይ፤ ይቀጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጠሃቸው።
13 ዐይኖችህ ክፉውን እንዳያዩ እጅግ ንጹሓን ናቸው፤አንተ በደልን መታገሥ አትችልም፤ታዲያ፣ አታላዮችን ለምን ትታገሣለህ?ክፉው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠውስ፣ለምን ዝም ትላለህ?
14 አንተ ሰዎችን በባሕር ውስጥ እንዳለ ዓሣ፣ገዥ እንደሌላቸውም የባሕር ፍጥረታት አደረግህ።
15 ክፉ ጠላት ሁሉንም በመንጠቆ ያወጣቸዋል፤በመረቡ ይይዛቸዋል፤በአሽክላው ውስጥ ይሰበስባቸዋል፤በዚህም ይደሰታል፤ ሐሤትም ያደርጋል።
16 በእነርሱ ተዝናንቶ ይኖራልና፤ምግቡም ሰብቶአል።ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፤ለአሽክላውም ያጥናል።