1 እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስሙ፤ ስለ ሚደርስባችሁ መከራ አልቅሱ፤ ዋይ ዋይም በሉ።
2 ሀብታችሁ ሻግቶአል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል።
3 ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም በእናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል፤ ለመጨረሻው ዘመን ሀብትን አከማችታችኋል።
4 ልብ በሉ፤ እርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የአጫጆቹም ጩኸት ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው ጌታ ጆሮ ደርሶአል።
5 በምድርም ላይ በምቾትና በመቀማጠል ኖራችኋል፤ ለዕርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል።