2 ከእናንተ ዘንድ አንድ ነገር ብቻ ማወቅ እፈልጋለሁ፤ መንፈስን የተቀበላችሁት ሕግን በመጠበቅ ነው ወይስ የተሰበከላችሁን በማመን?
3 ይህን ያህል የማታስተውሉ ናችሁን? በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ ፍጹም ለመሆን ትጥራላችሁን?
4 በርግጥ ለከንቱ ከሆነ፣ ይህን ያህል መከራ የተቀበላችሁት እንዲያው ነውን?
5 እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጣችሁ፣ በእናንተም ዘንድ ታምራትን የሚሠራው ሕግን ስለ ጠበቃችሁ ነው ወይስ የሰማችሁትን ስላመናችሁ?
6 እስቲ አብርሃምን አስቡ፤ “እርሱ እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።”
7 እንግዲህ እነዚያ የሚያምኑት የአብርሃም ልጆች እንደሆኑ አስተውሉ።
8 መጽሐፍ፣ እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቅ አስቀድሞ በማየት፣ “አሕዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ” በማለት ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ አስታወቀው።