5 ሳኦል በሚልከው በማናቸውም ስፍራ፣ ዳዊት ተልእኮውን በሚገባ ይፈጽም ስለ ነበር፣ በሰራዊቱ ላይ ሾመው፤ ይህም ሕዝቡን በሙሉ፣ የሳኦልንም የጦር ሹማምት ደስ አሰኘ።
6 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ከገደለ በኋላ፣ ሰዎቹ ወደየቤታቸው በሚመለሱበት ጊዜ፣ ሴቶች ከበሮና መሰንቆ ይዘው እየዘፈኑ፣ እየጨፈሩና እልል እያሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመቀበል ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።
7 ሴቶቹም እንዲህ ሲሉ በመቀባበል ዘፈኑ፤“ሳኦል ሺህ ገደለ፤ዳዊት ግን ዐሥር ሺህ ገደለ።”
8 ሳኦል እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር አላስደሰተውም። እርሱም፣ “ለዳዊት ዐሥር ሺህ አሉለት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ! እንግዲህ መንግሥት እንጂ ሌላ ምን ቀረው” አለ።
9 ከዚያች ዕለት አንሥቶ ሳኦል ዳዊትን በቅናት ዐይን ይመለከተው ጀመር።
10 በማግስቱም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በኀይል መጣበት፣ በዚህ ጊዜ ዳዊት ወትሮ እንደሚያደርገው ሁሉ በገና ሲደረድር፣ ሳኦል በቤቱ ሆኖ ትንቢት ይናገር ነበር። ሳኦል በእጁ ጦር ይዞ ነበር፤
11 እርሱም፣ “ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ” ብሎ በማሰብ ጦሩን ወረወረበት፤ ዳዊት ግን ሁለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ።