1 ሳሙኤል 7:11-17 NASV

11 እስራኤላውያንም ከምጽጳ ወጥተው ፍልስጥኤማውያንን በየመንገዱ እየገደሉ ከቤትካር በታች እስካለው ስፍራ ድረስ አሳደዷቸው።

12 ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ ስሙንም “እግዚአብሔር እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው።

13 በዚህ ሁኔታ ፍልስጥኤማውያን ድል ስለ ተመቱ፣ የእስራኤልን ምድር ዳግመኛ አልወረሩም።ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር።

14 ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከአቃሮን እስከ ጌት የነበሩ ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱላት፤ ግዛታቸውም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ነፃ ወጣች፤ በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ሰላም ነበረ።

15 ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ እስራኤልን ይዳኝ ነበር።

16 በየዓመቱ በቤቴል፣ በጌልገላና በምጽጳ እየተዘዋወረ፣ በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።

17 ከዚያም በአርማቴም ወዳለው ቤቱ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ደግሞ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር። በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።