6 ካበላኋቸው በኋላ ጠገቡ፤በጠገቡ ጊዜ ታበዩ፤ከዚያም ረሱኝ።
7 ስለዚህ እንደ አንበሳ እመጣባቸዋለሁ፤እንደ ነብርም በመንገድ አደባባቸዋለሁ።
8 ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ፣እመታቸዋለሁ፤ እዘነታትላቸዋለሁ።እንደ አንበሳም ሰልቅጬ እውጣቸዋለሁ፤የዱር አራዊትም ይገነጣጥላቸዋል።
9 “እስራኤል ሆይ፤ በእኔ ላይ ስለ ተነሣህ፣ረዳትህንም ስለ ተቃወምህ ትጠፋለህ።
10 “ንጉሥንና አለቆችን ስጠኝ፤”ብለህ እንደ ጠየቅኸው፣ያድንህ ዘንድ ንጉሥህ የት አለ?በከተሞችህ ሁሉ የነበሩ ገዦችህስ የት አሉ?
11 በቊጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤በመዓቴም ሻርሁት።
12 የኤፍሬም በደል ተከማችቶአል፤ኀጢአቱም በመዝገብ ተይዞአል።