14 “ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤በፍቅር ቃል አነጋግራታለሁ።
15 በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ።በዚያም ከግብፅ እንደ ወጣችበት ቀን፣እንደ ልጅነቷም ጊዜ ትዘምራለች።
16 “በዚያ ቀን፣ ‘ባሌ’ ብለሽ፣ትጠሪኛለሽ” ይላል እግዚአብሔር።“ከእንግዲህም፣ ‘ጌታዬ’ ብለሽ አትጠሪኝም።
17 የበኣል አማልክትን ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ስሞቻቸው አይነሡም።
18 በዚያን ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፣በምድርም ላይ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረት ጋር፣ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ፤ሁሉም በሰላም እንዲኖሩ፣ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን፣ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።
19 ለእኔ እንድትሆኚ ለዘላለም አጭሻለሁ፤በጽድቅና በፍትሕ፣በፍቅርና በርኅራኄም አጭሻለሁ።
20 በታማኝነት አጭሻለሁ፤አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።