20 በታማኝነት አጭሻለሁ፤አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።
21 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በዚያ ቀን እኔ እመልሳለሁ፤ለሰማያት እመልሳለሁ፤እነርሱም ለምድር ምላሽ ይሰጣሉ፤
22 ምድርም ለእህል፣ለአዲስ የወይን ጠጅና ለዘይት ምላሽ ትሰጣለች፤እነርሱም ለኢይዝራኤል ምላሽ ይሰጣሉ።
23 ስለ ራሴ ስል በምድሪቱ እተክላታለሁ፤‘ምሕረትን ያላገኘ’ ብዬ የጠራሁትንም እምረዋለሁ፤‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብለው የተጠሩትንም፣ ‘ሕዝቤ’ እላቸዋለሁ፤እነርሱም፣ ‘አንተ አምላኬ ነህ’ ይላሉ።”