4 “ነገር ግን ማንም ሰው አይከራከር፤ማንም ሌላውን አይወንጅል፤በካህናት ላይ ክስን እንደሚያቀርቡ፣ሕዝብህ እንደዚያው ናቸውና።
5 ቀንና ሌሊት ትደናበራላችሁ፤ነቢያትም ከእናንተ ጋር ይደናበራሉ፤ስለዚህ እናታችሁን አጠፋታለሁ፤
6 ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል።“ዕውቀትን ስለናቃችሁ፣እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።
7 ካህናት በበዙ ቊጥር፣በእኔ ላይ የሚያደርጉት ኀጢአት በዝቶአል፤ክብራቸውንም በውርደት ለውጠዋል።
8 የሕዝቤ ኀጢአት ለመብል ሆኖላቸዋል፤ርኵሰታቸውንም እጅግ ወደዱ።
9 ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።
10 “ይበላሉ ግን አይጠግቡም፤ያመነዝራሉ ግን አይበዙም፤ እግዚአብሔርን በመተው፣ራሳቸውን