1 “እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ!እናንት እስራኤላውያን፤ አስተውሉ!የንጉሥ ቤት ሆይ፤ ስሙ!ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤በምጽጳ ወጥመድ፣በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።
2 ዐመፀኞች በግድያ በርትተዋል፤ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ።
3 ስለ ኤፍሬም ሁሉን ዐውቃለሁ፤እስራኤልም ከእኔ የተሰወረች አይደለችም፤ኤፍሬም፣ አንተ አሁን አመንዝረሃል፤እስራኤልም ረክሳለች።
4 “የሠሩት ሥራ፣ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱአይፈቅድላቸውም፤የአመንዝራነት መንፈስ በልባቸው አለ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁትም።