5 የእስራኤል ትዕቢት በራሷ ላይ ይመሰክራል፤እስራኤላውያንና ኤፍሬምም በኀጢአታቸው ይሰናከላሉ፤ይሁዳም ደግሞ አብሮአቸው ይሰናከላል።
6 እግዚአብሔርን ለመሻት፣የበግና የፍየል መንጋ እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸውን ነድተው ሲሄዱ፣እርሱ ስለ ተለያቸው፣ሊያገኙት አይችሉም።
7 ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም፤ዲቃሎች ወልደዋልና፤ስለዚህ የወር መባቻ በዓላቸው፤እነርሱንና ዕርሻቸውን ያጠፋል።
8 “በጊብዓ መለከትን፣በራማ እንቢልታን ንፉ፤በቤትአዌን የማስጠንቀቂያ ድምፅ አሰሙ፤‘ብንያም ሆይ፤ መጡብህ!’ በሉ።
9 በቅጣት ቀን፣ኤፍሬም ባድማ ይሆናል፣በእስራኤል ነገዶች መካከል፣በእርግጥ የሚሆነውን ዐውጃለሁ።
10 የይሁዳ መሪዎች፣የወሰን ድንጋዮችን እንደሚነቅሉ ሰዎች ናቸው፤እንደ ጐርፍ ውሃ፣ቊጣዬን በላያቸው ላይ አፈስሳለሁ።
11 ጣዖትን መከተል በመውደዱ፣ኤፍሬም ተጨቊኖአል፤በፍርድም ተረግጦአል።