1 “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤እርሱ ሰባብሮናል፤እርሱም ይጠግነናል፤እርሱ አቊስሎናል፤እርሱም ይፈውሰናል።
2 ከሁለት ቀን በኋላ ያነቃናል፤በእርሱም ፊት እንድንኖር፣በሦስተኛው ቀን ያስነሣናል።
3 እግዚአብሔርን እንወቀው፤የበለጠ እናውቀውም ዘንድ እንትጋ፤እንደ ንጋት ብርሃን፣በእርግጥ ይገለጣል፤ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
4 “ኤፍሬም ሆይ፤ ምን ላድርግህ?ይሁዳ ሆይ፤ ምን ላድርግህ?ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ጉም፣እንደሚጠፋም የጧት ጤዛ ነው።
5 ስለዚህ በነቢያቴ ቈራረጥኋችሁ፤በአፌም ቃል ገደልኋችሁ፣ፍርዴም እንደ መብረቅ በላያችሁ አበራ።
6 ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፣ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እሻለሁና።