7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ገዦቻቸውን ፈጁ፤ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም።
8 “ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤ኤፍሬም ያልተገላበጠ ቂጣ ነው።
9 እንግዶች ጒልበቱን በዘበዙ፤እርሱ ግን አላስተዋለም።ጠጒሩም ሽበት አወጣ፤እርሱ ግን ልብ አላለም።
10 የእስራኤል ትዕቢት በራሱ ላይ መሰከረበት፤ይህ ሁሉ ሆኖ ግን፣ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤እርሱንም አልፈለገም።
11 ኤፍሬም በቀላሉ እንደምትታለል፣አእምሮም እንደሌላት ርግብ ነው፤አንድ ጊዜ ወደ ግብፅ ይጣራል፤ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አሦር ይዞራል።
12 ሲበሩ፣ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤እንደ ሰማይ ወፎችም ጐትቼአወርዳቸዋለሁ፤ስለ ክፉ ሥራቸውም በጒባኤ መካከል እቀጣቸዋለሁ።
13 ወዮ ለእነርሱ፤ከእኔ ርቀው ሄደዋልና!ጥፋት ይምጣባቸው!በእኔ ላይ ዐምፀዋልና።ልታደጋቸው ፈለግሁ፤እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።