3 ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ናቁ፤ጠላትም ያሳድዳቸዋል።
4 ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤እኔንም ሳይጠይቁ አለቆችን መረጡ፤በብራቸውና በወርቃቸው፣ለገዛ ጥፋታቸው፣ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።
5 ሰማርያ ሆይ፤ የጥጃ ጣዖትሽን ጣይ፤ቊጣዬ በእነርሱ ላይ ነድዶአል፤የማይነጹት እስከ መቼ ነው?
6 ይህም በእስራኤል ሆነ!ባለ እጅ የሠራው ይህ ጥጃ፣ አምላክአይደለም፤ያ የሰማርያ ጥጃ፣ተሰባብሮ ይደቃል።
7 “ነፋስን ይዘራሉ፤ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤አገዳው ዛላ የለውም፤ዱቄትም አይገኝበትም፤እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ባዕዳን ይበሉታል።
8 እስራኤል ተውጠዋል፤በአሕዛብም መካከል፣ዋጋ እንደሌለው ዕቃ ሆነዋል።
9 ለብቻው እንደሚባዝን የዱር አህያ፣ወደ አሦር ሄደዋልና፤ኤፍሬም በእጅ መንሻ ወዳጅ አበጀ።