13 ኤፍሬምን እንደ ጢሮስ፣በመልካም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፤አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን፣ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ ይሰጣል።”
14 እግዚአብሔር ሆይ፤ ስጣቸው፤ምን ትሰጣቸዋለህ?የሚጨነግፉ ማሕፀኖችን፣የደረቁ ጡቶችን ስጣቸው።
15 “በጌልገላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሣ፣እኔ በዚያ ጠላኋቸው፤ስለሠሩት ኀጢአት፣ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ከእንግዲህም አልወዳቸውም፤መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸው።
16 ኤፍሬም ተመታ፤ሥራቸው ደረቀ፤ፍሬም አያፈሩም፤ልጆች ቢወልዱም እንኳ፣ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”