8 ነቢዩ ከአምላኬ ጋር ሆኖ፣የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ዳሩ ግን በመንገዱ ሁሉ ወጥመድ፣በአምላኩም ቤት ጠላትነት ይጠብቀዋል።
9 በጊብዓ እንደ ነበረው፣በርኵሰት ውስጥ ተዘፍቀዋል፤እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፤ስለ ኀጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።
10 “እስራኤልን ማግኘቴ፣የወይንን ፍሬ፣ በምድረ በዳ የማግኘት ያህል ነበር፤አባቶቻችሁንም ማየቴ፣የመጀመሪያውን የበለስ ፍሬ የማየት ያህል ነበር፤ወደ ብዔልፌጎር በመጡ ጊዜ ግን፣ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ራሳቸውን ለዩ፤እንደ ወደዱትም ጣዖት የረከሱ ሆኑ።
11 የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤መውለድ፣ ማርገዝና መፀነስ የለም።
12 ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳ፣ልጅ አልባ እስኪሆኑ ድረስ እነጥቃቸዋለሁ፤ፊቴን ከእነርሱ በመለስሁ ጊዜ፣ወዮ ለእነርሱ
13 ኤፍሬምን እንደ ጢሮስ፣በመልካም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፤አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን፣ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ ይሰጣል።”
14 እግዚአብሔር ሆይ፤ ስጣቸው፤ምን ትሰጣቸዋለህ?የሚጨነግፉ ማሕፀኖችን፣የደረቁ ጡቶችን ስጣቸው።