14 ውዴ ለእኔ ከዓይንጋዲ የወይን ተክል ቦታ፣እንደ መጣ የሄና አበባ ዕቅፍ ነው።
15 ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽእንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽዐይኖችሽም እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው።
16 አንተ ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነህእንዴትስ ታምራለህዐልጋችንም እንደ ለምለም ሣር ነው።
17 የቤታችን ተሻካሚዎች ዝግባዎች፣የጣራችን ማዋቀሪያዎችም ጥዶች ናቸው።