ማሕልየ መሓልይ 7 NASV

1 አንቺ የልዑል ልጅ ሆይ፤ነጠላ ጫማ የተጫሙ እግሮችሽእንዴት ያምራሉ ሞገስን የተጐናጸፉ ዳሌዎችሽ፣ብልኅ አንጥረኛ የተጠበባቸውን የዕንቊ ሐብል ይመስላሉ።

2 ዕንብርትሽ ጥሩ የወይን ጠጅ እንደ ማይጐድልበት፣እንደ ክብ ጽዋ ነው፤ወገብሽ ዙሪያውን በውብ አበባ የታሰረየስንዴ ክምር ይመስላል።

3 ሁለት ጡቶችሽ፣መንታ የዋልያ ግልገሎችን ይመስላሉ።

4 ዐንገትሽ በዝሆን ጥርስ እንዳጌጠ መጠበቂያ ማማ ነው፤ዐይኖችሽ በባትረቢ በር አጠገብ እንዳሉት፣እንደ ሐሴቦን ኵሬዎች ናቸው፤አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ እንደሚመለከት፣እንደ ሊባኖስ መጠበቂያ ማማ ነው።

5 የራስሽ ቅርጽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ አክሊል ሆኖልሻል፤ጠጒርሽ የሐር ጒንጒን የመሰለ ነው፤ንጉሡም በሹሩባሽ ታስሮ ተይዞአል።

6 እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ የምትይ ነሽ!ፍቅሬ ሆይ፤ የምታስደስቺ ነሽ።

7 ቁመናሽ እንደ ዘንባባ ዛፍ መለል ያለ ነው፤ጡቶችሽም የፍሬውን ዘለላ ይመስላሉ።

8 እኔም፣ “የዘንባባውን ዛፍ እወጣለሁ፤ዘለላዎቹንም እይዛለሁ” አልሁ።ጡቶችሽ የወይን ዘለላ፣የእስትንፋስሽም መዐዛ እንደ እንኰይ ፍሬ ይሁኑ፤

9 ከናፍሮችሽም እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ይጣፍጡ።የወይን ጠጁ በቀስታ እየተንቈረቈረ፣ወደ ውዴ ከንፈሮችና ጥርሶች ይውረድ።

10 እኔ የውዴ ነኝ፤የእርሱም ምኞት እኔው ነኝ።

11 ውዴ ሆይ፤ ና ወደ ገጠር እንሂድ፤ወደ መንደርም ገብተን እንደር፤

12 ማልደን ወደ ወይኑ ተክል ቦታ እንሂድ፣ወይኑ እንቡጥ አውጥቶ፣አበባው ፈክቶ፣ሮማኑ አፍርቶ እንደሆነ እንይ፤በዚያም ራሴን በፍቅር እሰጥሃለሁ።

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8