ማሕልየ መሓልይ 1:2-8 NASV

2 በከንፈሩ መሳም ይሳመኝፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛልና።

3 የሽቱህ መዐዛ ደስ ያሰኛል፤ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነው፤ታዲያ ቈነጃጅት ቢወዱህ ምን ያስደንቃል

4 ይዘኸኝ ሂድ፤ እንፍጠን፤ንጉሡ ወደ ዕልፍኞቹ አምጥቶኛል።በአንተ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፤ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እንወድሳለን።አንተን እንደዚህ ማፍቀራቸው ትክክል ነው።

5 እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤እኔ ጥቊር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ጥቊረቴ እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎችም ነው።

6 ጥቊር ስለ ሆንሁ ትኵር ብላችሁ አትዩኝ፤መልኬን ያጠቈረው ፀሓይ ነውና፤የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ተቈጡኝ፤የወይን ተክል ቦታዎችም ጠባቂ አደረጉኝ፤የራሴን የወይን ተክል ቦታ ተውሁት።

7 ውዴ ሆይ፤ መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣በቀትርም የት እንደምትመስጋቸውእባክህ ንገረኝ፤በወዳጆችህ መንጎች ኋላ፣ፊቷን ሸፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?

8 አንቺ ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ የተዋብሽ ሆይ፤ የማታውቂ ከሆነ፣የበጎቹን ዱካ ተከተዪ፤የፍየል ግልገሎችሽንም፣በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።