1 እኔ የሳሮን ጽጌረዳ፣የሸለቆም አበባ ነኝ።
2 በእሾኽ መካከል እንዳለ ውብ አበባ፣ውዴም በቈነጃጅት መካከል እንዲሁ ናት።
3 በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ እንኰይ፣ውዴም በጐልማሶች መካከል እንዲሁ ነው፤በጥላው ሥር መቀመጥ ደስ ያሰኛል፤የፍሬውም ጣፋጭነት ያረካኛል።
4 ወደ ግብዣው አዳራሽ ወሰደኝ፤በእኔ ላይ ያለው ዐላማው ፍቅር ነው።
5 በዘቢብ አበረታቱኝ፤በእንኰይም አስደስቱኝ፤በፍቅሩ ተይዤ ታምሜአለሁና።