3 ቀሚሴን አውልቄአለሁ፤ታዲያ እንዴት እንደ ገና ልልበስ?እግሬን ታጥቤአለሁ፤እንዴት እንደ ገና ላቈሽሸው?
4 ውዴ እጁን በበሩ ቀዳዳ አሾለከ፤ልቤም ስለ እርሱ ይታወክ ጀመር።
5 ለውዴ ልከፍትለት ተነሣሁ፤በከርቤ ነጠብጣብ የራሱት እጆቼ፣በከርቤም ፈሳሽ የተነከሩት ጣቶቼ፣የመወርወሪያውን እጀታ ያዙ።
6 ለውዴ ከፈትሁለት፤ውዴ ግን አልነበረም፤ ሄዶአል፤በመሄዱም ልቤ ደነገጠ፤ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ጠራሁት፤ ነገር ግን አልመለሰልኝም።
7 የከተማዪቱም ጠባቂዎች፣በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤እነዚህ የቅጥሩ ጠባቂዎች፣ደበደቡኝ፤ አቈሰሉኝ፤ልብሴንም ገፈፉኝ።
8 እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤እማጠናችኋለሁ፤ውዴን ካገኛችሁት፣ምን ትሉት መሰላችሁ?በፍቅሩ መታመሜን ንገሩት።
9 አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?