7 የከተማዪቱም ጠባቂዎች፣በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤እነዚህ የቅጥሩ ጠባቂዎች፣ደበደቡኝ፤ አቈሰሉኝ፤ልብሴንም ገፈፉኝ።
8 እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤እማጠናችኋለሁ፤ውዴን ካገኛችሁት፣ምን ትሉት መሰላችሁ?በፍቅሩ መታመሜን ንገሩት።
9 አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?
10 ውዴ ፍልቅልቅና ደመ ግቡ ነው፤ከዐሥር ሺሆችም የሚልቅ ነው።
11 ራሱ የጠራ ወርቅ፣ጠጒሩ ዞማ፣እንደ ቊራም የጠቈረ ነው።
12 ዐይኖቹ፣በጅረት አጠገብ እንዳሉ ርግቦች፣በወተት የታጠቡ፣እንደ ዕንቊም ጒብ ጒብ ያሉ ናቸው።
13 ጒንጮቹ የሽቱ መዐዛ የሚያመጡ፣የቅመማ ቅመም መደቦችን ይመስላሉ፤ከንፈሮቹም ከርቤ እንደሚያንጠባጥቡ፣ውብ አበቦች ናቸው።