2 ውዴ መንጋውን ለማሰማራት፣ውብ አበቦችንም ለመሰብሰብ፣የቅመማ ቅመም መደቦቹ ወዳሉበት፣ወደ አትክልት ቦታው ወርዶአል።
3 እኔ የውዴ ነኝ፤ ውዴም የእኔ ነው፤መንጋውንም በውብ አበቦች መካከል ያሰማራል።
4 ውዴ ሆይ፤ አንቺ እንደ ቴርሳ የተዋብሽ፣እንደ ኢየሩሳሌም ያማርሽ፣ዐርማቸውን እንደ ያዙ ወታደሮችም ግርማን የተጐናጸፍሽ ነሽ።
5 አስጨንቀውኛልና፣እባክሽ ዐይኖችሽን ከእኔ ላይ አንሺ፤ጠጒርሽ ከገለዓድ ተራራ የሚወርድ፣የፍየል መንጋ ይመስላል።
6 ጥርሶችሽከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።
7 ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጒንጮችሽ፣ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።
8 ሥልሳ ንግሥቶች፣ሰማንያ ቁባቶች፣ቊጥራቸውም የበዛ ደናግል ሊኖሩ ይችላሉ፤