1 በቊጣው በትር፣መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ።
2 ከፊቱ አስወጣኝ፤በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ።
3 በእርግጥ ቀኑን ሁሉ በመደጋገም፣እጁን በላዬ ላይ መለሰ።
4 እርሱ ሥጋዬንና ቈዳዬን አስረጀ፤ዐጥንቶቼንም ሰባበረ።
5 በምሬትና በድካም፣ቅጥር ሠራብኝ፤ ዙሪያዬንም ከበበኝ።