11 እግዚአብሔር ለመቅሠፍቱ መውጫ በር ከፈተ፤ጽኑ ቍጣውን አፈሰሰ፤መሠረትዋን እንዲበላ፣በጽዮን እሳት ለኰሰ።
12 ጠላቶችም ሆኑ ወራሪዎች፣የኢየሩሳሌምን በሮች ጥሰው ይገባሉ ብለው፣የምድር ነገሥታት፣ወይም ከዓለም ሕዝብ አንዳቸውም አላመኑም።
13 ይህ ግን ከነቢያት ኀጢአት፣ከካህናቷም መተላለፍ የተነሣ ሆኖአል፤በውስጧ፣የጻድቃንን ደም አፍስሰዋልና።
14 እንደ ታወሩ ሰዎች፣በየመንገዱ ላይ ይደናበራሉ፤ማንም ሰው ደፍሮ ልብሳቸውን መንካት እስከማይችል ድረስ፣በደም እጅግ ረክሰዋል።
15 ሰዎች “ሂዱ! እናንት ርኵሳን!” ብለው ይጮኹባቸዋል፤“ወግዱ! ወግዱ! አትንኩ!” ይሏቸዋል፤ሸሽተው በሚቅበዘበዙበትም ጊዜ፣በአሕዛብ መካከል ያሉ ሰዎች፣“ከእንግዲህ በዚህ መቀመጥ አይገባቸውም!” ይላሉ።
16 እግዚአብሔር ራሱ በትኖአቸዋል፤ከእንግዲህ ወዲያ አይጠብቃቸውም፤ካህናቱ አልተከበሩም፤ሽማግሌዎቹም ከበሬታ አላገኙም።
17 ከሁሉም በላይ በከንቱ ርዳታን ስንጠባበቅ፣ዐይኖቻችን ደከሙ፤ከግንብ ማማችን ላይ ሆነን፣ሊያድን ከማይችል ሕዝብ ርዳታ ጠበቅን።