23 መዘምራኑ የየዕለቱን ተግባራቸውን በሚቈጣጠረው በንጉሡ ትእዛዝ ሥር ነበሩ።
24 የይሁዳ ልጅ የዛራ ዘር የሆነው የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ ሕዝቡን በሚመለከት ጒዳይ ሁሉ የንጉሡ ተወካይ ነበር።
25 ከይሁዳ ሕዝብ ጥቂቱ በመንደሮችና በእርሻ ቦታዎች፣ በቂርያት አርባቅና በዙሪያዋ ባሉ መኖሪያዎቿ፣ በዲቦንና በመኖሪያዎቿ፣ በይቀብጽኤልና በመንደሮቿ ተቀመጡ፤
26 በኢያሱ፣ በሞላዳ፣ በቤትጳሌጥ፣
27 በሐጸርሹዓል፣ በቤርሳቤህና በመኖሪያዎቿ፣
28 በጺቅላግ፣ በምኮናና በመኖሪያዎቿ፣
29 በዓይንሪሞን፣ በጾርዓ፣ በየርሙት፣