ነህምያ 11:3-9 NASV

3 እንግዲህ በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃዪቱ መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ በዚህ ጊዜም በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ የተወሰኑ እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያን፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች እያንዳንዳቸው በተለያዩ ከተሞች ባለ በየራሳቸው ንብረት ላይ ተቀመጡ፤

4 ከይሁዳና ከብንያም ወገን የሆኑት የተቀሩት ሰዎች ደግሞ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ከይሁዳ ዘሮች፦ከፋሬስ ዘር የመላልኤል ልጅ፣ የሰፋጥያስ ልጅ፣ የአማርያ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የዖዝያ ልጅ አታያ፤

5 ከሴሎ ዘር የዘካርያስ ልጅ፣ የዮያሪብ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣ የፆዛያ ልጅ፣ የኮልሖዜ ልጅ፣ የባሮክ ልጅ መዕሤያ።

6 በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ዘሮች በጠቅላላ 468 ብርቱ ሰዎች ናቸው።

7 ከብንያም ዘሮች፦የየሻያ ልጅ፣ የኢቲኤል ልጅ፣ የመዕሤያ ልጅ፣ የቆላያ ልጅ፣ የፈዳያ ልጅ፣ የዮእድ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ፤

8 ተከታዮቹም ጌቤና ሳላይ 928 ወንዶች፤

9 የእነዚህም አለቃ የዝክሪ ልጅ ኢዩኤል ሲሆን፣ የሐስኑአ ልጅ ይሁዳ የከተማዪቱ “ሁለተኛ አውራጃ” የበላይ ነበር።