7 ከብንያም ዘሮች፦የየሻያ ልጅ፣ የኢቲኤል ልጅ፣ የመዕሤያ ልጅ፣ የቆላያ ልጅ፣ የፈዳያ ልጅ፣ የዮእድ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ፤
8 ተከታዮቹም ጌቤና ሳላይ 928 ወንዶች፤
9 የእነዚህም አለቃ የዝክሪ ልጅ ኢዩኤል ሲሆን፣ የሐስኑአ ልጅ ይሁዳ የከተማዪቱ “ሁለተኛ አውራጃ” የበላይ ነበር።
10 ከካህናቱ፦የዮያሪብ ልጅ ዮዳኤ፤ ያኪን፤
11 የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ፤
12 የቤተ መቅደሱን ሥራ ያከናወኑት ወንድሞቻቸው፣ 822 ሰዎች፤ የመልክያ ልጅ፣ የፋስኮር ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የአማሲ ልጅ፣ የፈላልያ ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤
13 ወንድሞቹ የሆኑት የየቤተ ሰቡ አለቆች 242 ወንዶች፤ የኢሜር ልጅ የምሺሌሞት ልጅ፣ የአሕዛይ ልጅ፣ የኤዝርኤል ልጅ አማስያ፤