8 ሌዋውያኑ ደግሞ ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋር የምስጋና መዝሙር ኀላፊ የሆነው መታንያ ነበሩ።
9 ወንድሞቻቸው የሆኑት በቅቡቅያና ዑኒም በአገልግሎት ጊዜ ከእነርሱ ትይዩ ይቆሙ ነበር።
10 ኢያሱ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂም ኤልያሴብን ወለደ፤ ኤልያሴብ ዮአዳን ወለደ፤
11 ዮአዳ ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ያዱአን ወለደ።
12 በዮአቂም ዘመን የካህናቱ ቤተ ሰብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ከሠራያ ቤተ ሰብ፣ ምራያ፤ከኤርምያስ፣ ሐናንያ፤
13 ከዕዝራ፣ ሜሱላም፤ከአማርያ፣ ይሆሐናን፤
14 ከሙሊኪ፣ ዮናታን፤ከሰብንያ፣ ዮሴፍ፤