8 ነነዌን ግን፣በሚያጥለቀልቅ ጐርፍ ያጠፋታል፤ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።
9 በእግዚአብሔር ላይ ምንም ቢያሤሩ፣እርሱ ያጠፋዋል፤መከራም ዳግመኛ አይነሣም።
10 በእሾህ ይጠላለፋሉ፤በወይን ጠጃቸውም ይሰክራሉ፤እሳትም እንደ ገለባ ይበላቸዋል።
11 ነነዌ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ላይ የሚያሤር፣ክፋትንም የሚመክር፣ከአንቺ ዘንድ ወጥቶአል።
12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ምንም ኀይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑም፣ይቈረጣሉ፤ ይጠፋሉም።ይሁዳ ሆይ፤ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ከእንግዲህ አላስጨንቅህም።
13 አሁንም ቀንበራቸውን ከዐንገትህ ላይ አንሥቼ እሰብራለሁ፤የታሰርህበትንም ሰንሰለት በጥሼ እጥላለሁ።”
14 አንቺ ነነዌ፤ እግዚአብሔር ስለ አንቺ እንዲህ ብሎ አዞአል፤“ስም የሚያስጠራ ትውልድ አይኖራችሁም፤በአማልክቶቻችሁ ቤት ያሉትን፣የተቀረጹትን ምስሎችና ቀልጠው የተሠሩትን ጣዖታት እደመስሳለሁ፤መቀበሪያህን እምስልሃለሁ፤አንተ ክፉ ነህና።